ብዙ ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ጤፋችን በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ እና ከፍተኛ የሙያ እውቀት ባላቸው አርሶ አደሮች በባህላዊ እና በተፈጥሮአዊ መንገድ ይመረታል፡፡ ለረጅም ጊዜ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረ ከወቅቱ ጋር የሚሄድ የአመራረት ዘዴ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለውን የጤፍ ምርት ያለማቋረጥ ያመርታሉ፡፡ እኛም ተመራጭ የሆኑ እህሎችን ብቻ ከምርት ቦታዎች በጥንቃቄ እንመርጣለን፡፡

ለዚህም የጉዞ ርቀት የጤፍ ዱቄታችን ጥራት እና የምግብነት ጥቅሙን ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ ስለሚችል የጤፍ ዱቄቱን በቀጥታ ከኢትዮጵያ እናስገባለን፡፡ እንዲሁም የርቀት ሁኔታ ተጽእኖ የማይደረግባቸውን የጤፍ ዘርን እንልካለን፡፡ እህሎቻችን በጥንቃቄ በባቡር ወይም በጭነት ተሽከርካሪ ከኢትዮጵያ ወደ ጁቡቲ ከገቡ በኋላ ወደ አውሮፓ ይጫናሉ፡፡ መዳረሻቸው ከደረሱ በኋላ በትኩስነታቸው በፈረንሳይ በሚገኙ ወፍጮ ቤታችን ከተፈጩ በኋላ በማቀነባበር ከጥቂት ቀናት በኋላ ለእርሶ የሚደርሱ ይሆናሉ፡፡ ይህ ዘዴ ደግሞ ትኩስነታቸውን፣የምግብነት ጠቀሜታቸውን እና ትክክለኛ የጤፍ መዓዛቸውን እንደጠበቀ ያረጋግጣል፡፡

በመጋዘናችን ውስጥ ያለቀለትን ዱቄት አንይዝም፣ የእርሶ ትእዛዝ ከደረሰን በኋላ ጤፋችን በፈረንሳይ በሚገኝ ወፍጮ ይፈጫል፡፡ እነዚህ የጤፍ እህሎች የጥንት ዘመን ተሻጋሪ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባሀል በመጠበቅ በባህላዊ ወፍጮ ይፈጫሉ፡፡ ይህ ደግሞ በውስጡ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በመጠበቅ ሁሉም የምግብነት ጠቀሜታዎቹን እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ በዚህ ደግሞ ዱቄቱ ዳቦ እና እንጀራ ለማዘጋጀት ተመራጭ ነው፡፡

የጤፍ እህላችን ወደ ውጭ ሀገር ከመላካችን በፊት ንጹውን ከገለባው እንለያለን፣ እናጸዳለን እንዲሁም በውስጡ ሙሉ በሙሉ እንፈትሸዋለን፡፡ ማንኛውም የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ደረጃቸውን የጠበቀ የጭነት አገልግሎት ለመስጠት ብቃት እንዳላቸው ለማረጋገጥ የምስክር ወረቀቶችን ያቀርባሉ፡፡ በእያንዳንዱ የምርት ሂደት ላይ ማለትም እህሉን በምናከማችበት ጊዜ ፣ በምንፈጭበት ጊዜ ፣ በወረቀት ከረጢቶች በምናሸግበት ጊዜ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ የምናደርግ ሲሆን የወረቀት ከረጢቱ ደግሞ ከሌሎች ፕላስቲክ ከረጢቶች የበለጠ ጥራት ያለው እና ለአካባቢ ምቹ ስለሆነ ነው፡፡
ከፍተኛ የሆነ ጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ምርቶቻችን ገለለተኛ እና እውቅና ባላቸው ላብራቶሪዎች ተመርምሮ የአውሮፓ የምግብ ደንብ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ የምርቶቻችን ይዘቶችን በተመለከተ እርሶ ማወቅ የሚገቦት ጉዳዮች በምርቶቻችን እሽግ እና በምርቶቻችን ድረ ገጾች ላይ በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ ይህ መረጃ ሁልጊዜ ከእርሶ ሀገር ብሔራዊ ቋንቋ የተተረጎሙ ናቸው፡፡

የጤፋችን የተፈጥሮ ይዘት /ኦርጋኒክ/ መሆኑ አልተረጋገጠም፡፡ ነገር ግን የተመረተው በባህላዊ መንገድ ነው አብዛኛው የጤፍ ምርቶቻችን የሚመጡት በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የኬሚካል ማዳበሪያ ወይም የጸረ ተባይ ኬሚካሎችን ሳይጠቀሙ በተፈጠሮ መንገድ ከሚያመርቱ አርሶ አደሮች የተገኘ ነው ያመጣነው፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥም ማለትም የጤፍ ምርታችን ሙሉ በሙሉ ከጎጂ ይዘቶች የፀዳ መሆኑን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ውስጥ እያንዳንዱ ጭነት ቦታ ላይ የላብራቶሪ ፍተሻ እናደርጋለን፡፡

እኛ ሁልጊዜ ምርቶቻችንን በተቻለ መጠን በፍጥነት ለማድረስ ዝግጁ ነን፡፡ ምርቱን ለማቅረብ የሚፈጀው ጊዜ የሚፈጭ የዱቄት መጠን እና የመጓጓዣ ርቀቱ ላይ የሚመሰረት ሲሆን ነገር ግን እኛ እርሶ የሚገኙበት ቦታ ከ3 እስከ 7 ቀናት ውስጥ እናደርሳለን፡፡ በፍላጎት መሰረት የሚፈጭ ዱቄት ከ2 እና 4 ቀናት ሊፈጅ የሚችል ሲሆን ማጓጓዣው ደግሞ እርሶ የሚኖርበት ሀገር የርቀት ሁኔታ መሰረት ከ24 ሰዓት እስከ 72 ሰዓት ሊሆን ይችላል፡፡ በፈረንሳይ አጠገብ በሚገኙ አካላት የሚታዘዙ ትናንሽ ትእዛዞች (እስከ 2 ቶን) ከ 3 እስከ 4 የስራ ቀናት ውስጥ እንዲደርሱ ይጠበቃል፡፡ ረጅም ጉዞ የሚጓዙ ትላልቅ ትእዛዞች ደግሞ ከ7 እስከ 10 ቀናት የሚፈጁ ናቸው፡፡

ዋጋችን የምርቱ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በእኛ ዘንድ ሁልጊዜ በገንዘብዎ ከፍተኛ የሆነ እሴት ያገኛሉ፡፡ ብዛቶን ከማስቀመጦት በፊት ስለዋጋው በተመለከተ info@aromaimpex.com ያነጋግሩን፡፡

ሌሎች ሻጮች በአፍሪካ ውስጥ የተፈጨውን የጤፍ ዱቄት ካስገቡ በኋላ ከመሸጡ በፊት ለወራት በመጋዘን ውስጥ የሚያስቀምጡ ሲሆን እኛ ግን የእርሶ ትእዛዝ ከደረሰን በኋላ የጤፍ እህልን በመፍጨት ትኩስ ዱቄት እናቀርባለን፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ዱቄታችን ሁልጊዜ ትኩስ እና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው ሲሆን በረጅም ጊዜ በመቀመጡ ምክንያት የተበላሸ አይደለም፡፡ ሌሎች ሻጮች ዱቄታቸውን በፕላስቲክ መያዣ ውስጥ የሚያሽጉ ሲሆን ይህ ደግሞ ለአካባቢ ምቹ አይደለም፡፡ እኛ ግን የጤፍ ዱቄታችንን ጥራት የሚጠብቅ እና የፕላኔታችንን ጤና የሚደግፍ የወረቀት ከረጢት እንጠቀማለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባህላዊ ዘዴ እና ጥራቱን የጠበቀ የወፍጮ የመፍጨት ዘዴ የምንጠቀም በመሆኑ የምርታችንን ጥራት፣ የተፈጥሮ መዓዛ የሚጠብቅ ሲሆን ይህ ደግሞ ትክክለኛ እንጀራ ለማዘጋጀት ተመራጭ ነው፡፡ ሁልጊዜ ለጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት እንሰጣለን፡፡ በፈረንሳይ ሀገር ውስጥ የሚገኝ ፋብሪካችን ታዳሽ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ እና የፀሀይ ሀይል ምንጮችን ይጠቀማሉ፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵውያ አርሶ አደሮች የውሀ ሀብታቸውን እና አካባቢያቸውን እንዲጠበቁ እናበረታታለን፡፡

እርሶ የግሮሰሪ ፣ የሬስቶራንት ፣ ዳቦ ቤት ወይም ካፌ ባለቤት ኖት ወይ? እንደዛ ከሆነ የምርቶቻችንን ናሙና መላክ እንችላለን፡፡

እያንዳንዱ የአሮማ ጤፍ ትእዛዝ ለእርሶ ሂሳብ ስለሚያስፈልግ ከደረሰኝ ትእዛዝ ዝርዝር ጋር ይመጣል