ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የነጭ እና ቀይ ጤፍ ዱቄታችን በስተጀርባ ያለው ሚስጥር
የኢትዮጵያ ጤፍ

- ተመራጭ የጤፍ እህል ለማምረት በቀጥታ ከአርሶ አደሮች ጋር እንሰራለን፡፡
- ተመራጭ የሆነ ትኩስ ዱቄት ለእርሶ ለማድረስ ትእዛዝ እኛ ጋር ከደረሰ በኋላ በፈረንሳይ ሀገር ከሚገኝ ወፍጮ ቤታችን መፍጨት እንጀምራለን፡፡
- የዱቄት ምርታችን በኢትዮጵያ ባህል ስርአት እና የአውሮፓ የጥራት ደረጃን በመከተል በጥንቃቄ እናመርታለን፡፡
- በጥሩ ሁኔታ የተፈጨ የጤፍ ዱቄት ለብዙ ተጨማሪ የምግብ አዘገጃጀት ዘዴዎች ያለው ጥቅም በተጨማሪ የእንጀራ እና ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ለመስራት ምርጥ ነው፡፡
የጤፍ ምርታችን እንዲፈጭላችሁ ትእዛዝ ስታቀርቡ ብቻ ወዲያውኑ እንፈጫለን፡፡ በዚሁ መሰረት እንደፍላጎቶ ትኩስ ዱቄት ባለ 1ኪግ፣ 5ኪግ፣ ወይም 25ኪግ ባሉበት እናቀርባለን፡፡ ዱቄታችን ተመራጭ የሆነ እንጀራ ለመጋገር ከፍተኛ ጥራት አለው፡፡
የእኛ ምርቶች
ተመራጭ የሆነ እንጀራ ለማዘጋጀት
ስለ እኛ
እኛ የሲዊዘርላንድ እና የኢትዮጵያ ዜጋ ሆነን ጂን ዶሚኒክ እና መዓዛ ሙሉጌታ ልህማን የተባልን ሲሆን በሲዊዘርላንድ ሀገር ጄኔቫ ከተማ እንኖራለን፡፡ መዓዛ ሙሉጌታ ልህማን በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ሲሆን የሀበሻ ምግብ አዘገጃጀት ዘዴ የህይወቷ መሰረት እና ባህሏ ነው፡፡ ጂን ደግሞ ለተወሰኑ አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር በነበረበት ጊዜ ከኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ጋር ጥሩ ግንኙነት አዳብሯል፡፡ ራእያችን የባህል እሴቶችን በማክበር የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት ዘዴ መደገፍ እና ማስተዋወቅ ነው፡፡

ብዙ ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
ጤፋችን በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ እና ከፍተኛ የሙያ እውቀት ባላቸው አርሶ አደሮች በባህላዊ እና በተፈጥሮአዊ መንገድ ይመረታል፡፡ ለረጅም ጊዜ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረ ከወቅቱ ጋር የሚሄድ የአመራረት ዘዴ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለውን የጤፍ ምርት ያለማቋረጥ ያመርታሉ፡፡ እኛም ተመራጭ የሆኑ እህሎችን ብቻ ከምርት ቦታዎች በጥንቃቄ እንመርጣለን፡፡
ለዚህም የጉዞ ርቀት የጤፍ ዱቄታችን ጥራት እና የምግብነት ጥቅሙን ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ ስለሚችል የጤፍ ዱቄቱን በቀጥታ ከኢትዮጵያ እናስገባለን፡፡ እንዲሁም የርቀት ሁኔታ ተጽእኖ የማይደረግባቸውን የጤፍ ዘርን እንልካለን፡፡ እህሎቻችን በጥንቃቄ በባቡር ወይም በጭነት ተሽከርካሪ ከኢትዮጵያ ወደ ጁቡቲ ከገቡ በኋላ ወደ አውሮፓ ይጫናሉ፡፡ መዳረሻቸው ከደረሱ በኋላ በትኩስነታቸው በፈረንሳይ በሚገኙ ወፍጮ ቤታችን ከተፈጩ በኋላ በማቀነባበር ከጥቂት ቀናት በኋላ ለእርሶ የሚደርሱ ይሆናሉ፡፡ ይህ ዘዴ ደግሞ ትኩስነታቸውን፣የምግብነት ጠቀሜታቸውን እና ትክክለኛ የጤፍ መዓዛቸውን እንደጠበቀ ያረጋግጣል፡፡
በመጋዘናችን ውስጥ ያለቀለትን ዱቄት አንይዝም፣ የእርሶ ትእዛዝ ከደረሰን በኋላ ጤፋችን በፈረንሳይ በሚገኝ ወፍጮ ይፈጫል፡፡ እነዚህ የጤፍ እህሎች የጥንት ዘመን ተሻጋሪ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባሀል በመጠበቅ በባህላዊ ወፍጮ ይፈጫሉ፡፡ ይህ ደግሞ በውስጡ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በመጠበቅ ሁሉም የምግብነት ጠቀሜታዎቹን እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ በዚህ ደግሞ ዱቄቱ ዳቦ እና እንጀራ ለማዘጋጀት ተመራጭ ነው፡፡