እኛ የሲዊዘርላንድ እና የኢትዮጵያ ዜጋ ሆነን ጂን ዶሚኒክ እና መዓዛ ሙሉጌታ ልህማን የተባልን ሲሆን በሲዊዘርላንድ ሀገር ጄኔቫ ከተማ እንኖራለን፡፡ መዓዛ ሙሉጌታ ልህማን በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ሲሆን የሀበሻ ምግብ አዘገጃጀት ዘዴ የህይወቷ መሰረት እና ባህሏ ነው፡፡ ጂን ደግሞ ለተወሰኑ አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር በነበረበት ጊዜ ከኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ጋር ጥሩ ግንኙነት አዳብሯል፡፡ ራእያችን የባህል እሴቶችን በማክበር የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት ዘዴ መደገፍ እና ማስተዋወቅ ነው፡፡